Wednesday, January 16, 2013

ታሪክ ይፍረደን! እውነት ይፍረደን! ጊዜ ይፍረደን!

Ethiopian journalist Abebe Gellaw discussed on the foiled assassination plot against him on ''Netsanet Le Ethiopia'' radio.

Netsanet Le Ethiopia Radio

’’ይኼ ያለፈው 21 ዓመት ሀገራችን ውስጥ ምን እንደተፈጠረ ተደጋግሞ መወራት የለበትም፤ ታውቃላችሁ። ህዝባችን ምን ዓይነት ጣጣ ውስጥ እንዳለ፤ ሀገር ምን ዓይነት ችግር ውስጥ እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን፤ እናም ሁላችንም በተቻለ መጠን ያንን ስቃይ ያለበትን ህዝብ፣ ለራሳችንም ቢሆን ለነፃነታችን ኡኡ ማለት አለብን፤ በምንችለው። ይኼ ህሊና ላለው ሰው ነው የምለው፤ ሁላችንም ይኼን ማድረግ አለብን። ይኼንን ግን ጠንቅቆ ከመጀመሪያው ጀምሮ ይህንን ሲታገሉ ከነበረና አሁንም እየታገለ ለዚህ ደግሞ ብዙ፣ ብዙ ዋጋ እየከፈለ ያለ አንድ ወንድማችን አለ። እሱ ነው እንግዳችን። ይህንን እንግዳችን እስቲ አየር ላይ እንዳለ በመጀመሪያ በእናንተ ስም፣ በኔ ስም እንዳመሰግነው እስቲ በመጀመሪያ መስመር እንዳለ ልሞክር። ጤና ይስጥልኝ አቶ አበበ!እንደምን አለህ?ደህና ነህ? በጣም አበበ በጣም፣ በጣም ነው የማመሰግነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ይኼ ያሉትን ሁኔታዎች፣ የተፈጠረውን ሁኔታ እንድታስረዳን ጠይቄህ እሺ ብለህ፤ ይኸውና በመስመር ላይ በታይሙ መጥተህ ስላገኘንህ፣ ስለተቀበልክልን በጣም፣ በጣም ነው የማመሰግነው፤ በእኔም በአድማጮቼ ስም በጣም፣ በጣም አመሰግንሀለሁ።’’

Abebe Gellaw

’’እነዚህ ፅንፈኞቹ ግን መለስ ዜናዊን እንደ ጣዖት ነበር የሚያመልኩት፤ ትልቅ ጣዖት ነበር ለነሱ። ከሱ በላይ መሪ የለም፤ ከሱ በላይ ሰው የለም። እሱ ልክ በእግዚአብሔር ደረጃ አስቀምጠውት የነበረበት ሁኔታ ነበር ያለው። እኔ እንግዲህ ያደረግኩት ተቃውሞ የፈጠረባቸው ነገር ምንድን ነው፤ ያንን ጣዖት ፈጠፈጠው፣ የኔ ተቃውሞ የዛን ጣዖት ክብር ገፈፈው፣ ወደቀ፣ ጣዖቱ ተከሰከሰ፣ ብሎም ደግሞ በእግዚአብሔር እርዳታ ደግሞ አለፈ፣ ሞተ። እና ይኼ ከፍተኛ የሆነ ህመም ፈጥሮባቸዋል። እኛ ደግሞ በጣዖት ስለማናምን፤ እኛ በጣዖት የማናመልከው ሰዎች እፎይታ ነው የተሰማን። ምክንያቱም እነዚህ ጣዖቶ አምላኪዎች ናቸው ኢትዮጵያን ጠፍንገው ይዘው፣ እንደዚህ ዓይነት አስከፊ የሆነ ጭቆናና ረገጣ እያደረጉብን ያለው። የዚህ የጣዖት፣ የነሱ ጣዖት መውደቅና መከስከስ ኢትዮጵያ በከፊል ነፃ እንደወጣች ነው እኔ በበኩሌ የምቆጥረው። የቀረው ትንሽ ነው፤ እንጂ ሥራዓቱ በሙሉ ነው የተናጋበት ሁኔታ የተፈጠረው። ምክንያቱም በጣዖት ላይ የተመሰረተ፣ በግለሰብ አምልኮ ላይ የተመሰረተ፣ በግለሰብ ስብዕና ዙሪያ የተመሰረተ ስርዓት ስለ ነበር መገርሰሱና ያም ደግሞ በማያዳግም ሁኔታ፣ ተመልሶ በማይመጣበት ሁኔታ ማክተሙ ለነሱ ከፍተኛ የሆነ ህመም ፈጥሮባቸዋል። እና ለኛ ደግም ከፍተኛ የሆነ ደስታ ፈጥሮልናል። እኛ ስንደሰት ነው፤ እነሱ እንግዲህ ፀጉራቸውን እየነጩ፣ ፊታቸውን እየቦጫጨቁ በሰዎች ላይ ጥቃት እንሰነዝራለን እያሉ የሚንቀሳቀሱት በዚህ ምክንያት ነው።

እኛ ደግሞ በጋራ ይህንን መመከት መቻል አለብን። በጋራ ልተንቀሳቀስን ይኼ በግል የምናደርገው ትግል ዋጋ የለውም። አሁን ከዚህ በኋላ ማሰብ ያለብን በጋራ ተንቀሳቅሰን፣ ያንዱ ጥቃት የሌላው ጥቃት መሆን አለበት። በኔ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት፤ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ሊሆን ይገባዋል። ምክንያቱም እኔ ድምፄንም ያሰማሁት ስለ እኔ አይደለም። ስለ ሀገሬ፣ ስለ ህዝቤ ነው። እኔ ለህዝቤ እጅግ ነው የምቆረቆረው፣ ለሀገሬ በጣም ነው የምቆረቆረው። ህዝቤን እወዳለሁ፣ አገሬን እወዳለሁ። ሀገርና ሕዝብ መውደድ ለነሱ ወንጀል ስለሆነ፤ እኔንም ሊያጠቁኝ የሚፈለገው ሀገር ወዳዱን ሕዝብ ለማሸማቀቅ ስለፈለጉ ነው። ስለ ሀገሩ የጮኸ ሁሉ፣ እነሱን የደፈረ ሁሉ እንደሚመታ ሊያሳዩን ስለሚፈልጉ ነው። እና በጋራ ነው መከላከል የሚገባን። አንዱ ሲጠቃ ሌላው መመከት አለበት። በጋራ ከቆምን እነዚህን ወንበዴዎች (በውንብድና ነው መቸም ሀገራችንን እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሷት፤ ምንም ህግና ሥራዓት የሚያውቁ ሰዎች አይደሉም፤ ያውሬ ባሕርይ ነው የሚያሳዩት) እነዚህን አውሬዎች በአግባቡ ከሀገራችን ማስወግውድ የምንችልበትንና የሕዝባችንን ደግሞ ነፃነት ማረጋገጥ የምንችልበትን ጊዜ ማቃረብ የምንችለው በጋራ ስንቋቋማቸው ብቻ ነው።

እና አሁንም እንዳልኩት በኔ ላይ ይህን ያህል ጥላቻና እኔንም ደግሞ ለማጥፋት እየሞከሩ ያሉት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ጥማት ለማፈን ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጋር አብሮ ጎን ለጎን መታየት ይገባዋል። እኔን በግሌ አይደለም የመጡብኝ። እኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ድምፅ በማሰማቴ ብቻ ነው። ሌላ ምንም ምክንያት የለውም። በግል እኔ ብዙ ነገር ስፅፍ ነበር መለስ ዜናዊ ላይ፤ ብዙ ነገር ስናገር ነበር። የዛን ጊዜ ከመጤፍም አይቆጥሩኝም ነበር። እንኳን አያደለም በዚህ ደረጃ ትኩረት ሊሰጡኝ። አሁን ግን ጩኸቱ ወጥቶ በአለም አቀፍ አደባባይ የተሰማበትና እሱም ደግሞ ተሸማቆ በዛው የተሰናበተበት ሁኔታ መፈጠሩ፤ ለነሱ ትልቅ ህመም ነው የፈጠረባቸው። እሰየሁ ነው የምንለው እኛ፤ ትግላችንን ደግሞ አጠናክረን መቀጠል ነው የሚያስፈልገን።’’
To litsen to the discussion:

No comments:

Post a Comment