Tuesday, January 22, 2013

ምስጢራዊው የበረሃው ሲኖዶስና የማህበረ ቅዱሳን ፓትርያርክ

ከአብየ አዲ - አዲስ አበባ
21 January 2013


ከቤተ ማህቶት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በተመለከተ፤ ለሰሚ የሚገርሙ ዜናዎች መስማት ከተጀመረ ከርሟል። ግን ቤተ ክርስቲያኗ እንዲህ ትሆን ዘንድ ከበረሃ ጀምሮ የተጠነሰሰና የታቀደ ረቂቅ ዕቅድ መኖሩና፤ አሁንም እየተተገበረ ያለው ያ መሆኑን በርካታ ዜጎች ያወቁ አይመስልም። ህወኅት በረሃ እያለ በ1980ዎቹ ውስጥ ፓትሪያርክ እንዳዘጋጀ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?። ቤተ ክርስቲያኗን እስከወዲያኛው ለመቆጣጠር የህወኅት ካድሬዎች ጳጳሳት ሆነው የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ መውቅር ላይ እንዲቀመጡ ተደርጓል። ሌላም ሌላም። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኢህአዴግ ቅኝ ግዛት ውስጥ እንዴት እንደወደቀች በማስረጃ እንመልከት። ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ ነውና ከመጀመሪያው እንጀምር። የመጀመሪያው መጀመሪያ።

ዘመቻ ኦርቶዶክስ - ኅወሃትና ለቤተ ክርስቲያኗ የደገሰው የሞት ድግስ

የትግራይን ብሔርተኝነት(Tigray Ethnicism)አንግቦ የተነሳው ኅዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ፤ ይከተል የነበረው ርእዮተ ዓለም(Marxism)ማርክሲዝም ሌኒንዝም ነበር። ሲጀምር ማርክሲዝም ፀረ ሃይማኖትና ሃይማኖትን ማዋረድና ማራከስ ዓላማው የሆነ ፖለቲካዊ እሳቤ ነው። ከዚያ ፍልስፍና በመነሳት ይኼ ድርጅት ታሪካውቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ’’ፊውዳልና መመታት ያለባት’’ አድርጎ ፈረጀ ሲቀጥል ደግሞ ኅወሃት ብሔርተኝነት(Ethnicity)ላይ እንጂ ብሔራዊነት ወይም አሀዳዊነት (Unitary) ወይም አንድነት ላይ ንቀት የነበረበት ድርጅት ስለነበረ፤ ያገሪቱ አንድነትን የሚያንፀባርቁ ድርጅቶችን በሙሉ እንደ ጠላት የማየት አባዜ የነበረበትና አሁንም ያለበት ድርጅት ነው። ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ኅብረ ብሔራዊት መሆኗ ኅወሃት ጥርስ ውስጥ ለመግባት በቂ ምክንያት ነበር። ይህንንም የኅወሃት መስራችና የቀድሞ መሪ የነበሩት ዶክተር አረጋዊ በርሄ A political history of the Tigray People’s Liberetion Front (1975–1991): Revolt, Ideology and Mobilization in Ethiopia በሚለው ለዶክትሬት ማሟያ በፃፉት ድርሳናቸው ውስጥ እንዲህ ሲሉ በማያወላዳ ቋንቋ ገልፀውታል።
The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country. It also understood a possible alliance between the church and forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as against separatism. The church was viewed as a force standing against the way of the TPLF but one that should be handled with caution. There was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause.

ይህንንም ዓላማ ዳር ለማድረስ የተጠቀመበት መሰሪ ዘዴ፤

1ኛ የቤተ ክርስቲያን ሰው መስሎ አብያተ ክርስቲያናቱ ውስጥ መሰግሰግ፤

2ኛ በትልልቅ ገዳማት መነኮሳትንና ካህናትን በማሳሳት ለኅወሃት ፀረ ቤተ ክርስቲያን ዓላማ ተገዢ ማድረግና

3ኛ ለዘለቄታው ቤተ ክርስቲያኗን ለማሽመድመድና በቁጥጥሩ ስር ለማስገባት የራሱን ካድሬዎች ሲኖዶስና ከፍተኛ አመራር ውስጥ በማስገባት ሙሉ በሙሉ ቤተ ክርስቲያኗን መቆጣጠር ነው። እያንዳንዱን በደጋፊ መረጃ እንመልከት፤

የኅወሃት ካድሬዎች ገዳም መግባት

የኅወሃትን ታሪክ ከፃፉት ጥቂት ሰዎች መካከል ለአሜሪካ የመረጃ ድርጅት ቅርበት እንዳላቸው የሚታመነው John Young, Peasant Revolution in Ethiopia: The Tigray People Libertion Front (1975-1991)በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 176 ላይ የኅወሃት ካድሬዎች ላሰቡት ስውር ዓላማችው እንዲረዳቸው የቤተ ክርስቲያኗን ትምህርት ማጥናት እንደጀመሩ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል፤
‘’TPLF cadres spent considerable time studying the Bible and the teaching of the church so as to equip themselves for the task’’
እነዚሁ በዓላማ የቤተ ክርስቲያኗን ትምህርት እንዲያጠኑና መነኩሴ እንዲመስሉ የሰለጠኑት የኅወሃት ካድሬዎች በአቶ  ስብሃት ነጋ በሚመራ የስለላ መዋቅር በየገዳማቱ እንዲበተኑ እንደተደረገና ፤ እነዚህም ሰላይ የድርጅት አባላት የየገዳማቱን ቁልፍ ቦታ እንዲይዙና መንፈሰ ልል መነኮሳትን እንዲመለምሉ መደረጉን ሁኔታውን ባይናቸው ያዩትና በወቅቱ የድርጅቱ ሰብሳቢ የነበሩት ያሁኑ ዶክተር አረጋዊ በርሄ እንዲህ ሲሉ ነበር ያስቀመጡት፤
This process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church’s national hierarchy. To weaken church authority an intelligence group was formed under Sibihat Nega to infiltrate the well-established monasteries in Tigrai such as Debre Damo by planting TPLF members camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of the TPLF.

የጭቁን ካህናትና ሰላይ መነኮሳት መፈጠር

የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አጥንተው ፣ የቤተ ክርስቲያን ሰው መስለው ወደየገዳማቱ በመሄድ ስልጣን የተቆናጠጡት መለእክተኞች ቀስ በቀስ የአብያተ ክርስቲያናቱንና የገዳማቱን ማህበረሰብ ማሽከርከር ጀመሩ። የተቃወሟቸውን አባቶች በማስገደልና በማሳፈን ሌሎችንም በተለያየ ሁኔታ በማምታታት ባጭር ግዜያት ውስጥ  በርካታ ገዳማትና ትልልቅ አብያተ ክርስቲያናት የኅወሃት መጋለቢያ ምቹ ሜዳዎች ሆኑ። ጥቂቶችን ካህናትን የሃይማኖቱ ህግ ከሚፈቅደው ውጭ ጠመንጃ በማስታጠቅ ታጋይ ቀሳውስት ሲያደርጓቸው ሌሎቹን ደግሞ የስለላ መዋቅር ውስጥ በመሰግሰግ በተሳካ ሁኔታ ተዋጊ ካህናትና ሰላይ መነኮሳትን ለመፍጠር ቻሉ። ይህንንኑ ጉዳይ አጥብቆ የተመራመረው አሜሪካዊው ምሁርና የፖለቲታ ተንታኝ ፒተር ያንግ ይህን የካድሬ ካህናት ጉዳይ በሰፊው እንዲ ሲል ከመጀመሪያው አሳስቦ ነበር፤
Some priests rejected the church’s prohibition against taking up arms and became TPLF fighters, most were too old to take up with the youthful fighters and were more likely to join local militia or serve as teachers in front established schools… Some priests played an important role in introducing fighters to other priests and local people in recently liberated territories. Such priests told people that unlike the atheistic Derg, the TPLF was made up of true Christians.
Other priests assumed a similar role outside Tigray. Two such priests reported that they served in the TPLF for seventeen years as political cadres, not carrying guns but ’’agitating people’’ throughout newly liberated territories in Tigray and beyond to Gondar and Wello as the front took the struggle south in the final stages of the war. Since Amharigna and geez were the languages of the church they could be effectively employed throughout northern Ethiopia by priests. Following the TPLF, these ambassador-priests held meetings where fighters would be introduced to the priests of newly liberated territories as their ’’children’’ and always the contrast was made between the TPLF who came as liberators and the ’’atheist Derg’’. Older and respected priests would then be recruited from each area to carry word forth.

የበረሃው ቤተ ክህነትና የጫካው ሲኖዶስ ምስረታ

ቀስ በቀስ እነዚህ ታጣቂ ቀሳውስትና ‘’ጭቁን ነን’’ ባይ መንኮሳቶች የስራ አድማሳቸው እየሰፋ መጣ።  ቁጥራቸው እየአደገና እየተበራከተ መምጣቱን የተረዱት እነዚሁ አካላት በአካባቢያቸው ያሉትን አድባራትና ገዳማት ከመቆጣጠር አልፈው የቤተ ክርስቲያን ቀኖናን መደንገግ ጀመሩ። ከጥቂት ግዜያትም በኋላ የጫካውን ቤተ ክህነትና ሲኖዶስ ሊመሰርቱ ቻሉ።
 These conferences held near Abi Adi in 1983 and Roba kazi in 1984 did much to consolidate TPLF support from priesthood. Some 747 priests attended the first conference and 550 priests attended the second, at which delegates agreed to … . Significantly in the liberated territories, thus giving rise to a ‘’TPLF secretariat’’ and a ‘’Derg secretariat’’ which continued to function out of Mekele when Mekele was captured by the TPLF in 1989 the ‘’Derg supported’’ Tigrayan secretariat was transferred to Wello, and the TPLF-supported secretariat assumed responsibility for the administration of the whole Tigray.
ይህም የበረሃ ቤተ ክህነትና ሲኖዶስ ኅወሃት መቀሌን ሲቆጣጠር መንበሩን መቀሌ ላይ በማድረግ ‘’ነፃ የወጡ’’አካባቢዎች ቤተ ክህነት መምራት ጀመረ። ያዲስ አበባው የመቀሌ ሀገረ ስብከት ደግሞ ወደ ደሴ በመሸሽ መንበሩን ደሴ ላይ ተክሎ ግልጋሎቱን ቀጠለ። ደሴ በኅወሃት ሲያዝ ደግሞ ደሴ ቢሮ ከፍቶ የነበረው የትግራይ ሀገረ ስብከት ወደ አዲስ አበባ ሲሸሽ የጫካው ቤተ ክህነት ደግሞ ደሴ ላይ ስሩን ተከለ። ኅወሃት እየገፋም መጥቶ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ይኸው የጫካው ቤተ ክህነት አብሮ አዲስ አበባ ገባ። የጫካው ቤተ ክህነት ግን የራሱን ፓትሪያርክ መርጦ ጨርሶ ነበርና ቀጣይ ስራቸው ከተሾሙ ሶስት አመት ያልሞላቸውን ፓትሪያርክ መርቆርዮስንና መሰል አባቶችን ቦታ ማስለቀቅ ነበር።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጸሐፊ የነበሩት ሌንጮ ለታም ኅወሃት ገና ጫካ እያለ ሲኖዶስና ቤተ ክህነት መመስረቱን አልፎ ተርፎም ደግሞ ጳጳስ አዘጋጅቶ እንደነበረ፤ ‘’The Ethiopian State at the crossroads’’ በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ለዓለሙ ማህበረሰብ እንዲህ በማለት ገልፀው ነበር፤
Despite the fact that TPLF was an avowed Marxist-Leninist organization, it was engaged in conducting conferences in Tigrean clergy in the later part of 980s. One possible aim was to explore the selection of a new patriarch or Abuna…What is of importance of  the issue that we are dealing with is that an attempt was being made to create a new kind of relationship between the emerging authority and the institution of the church. The observable result was the emergence of a new kind of priest in TPLF held areas. A ‘’militant priest’’ was supposedly fashioned in the process, as distinct from the priest that still continued to stay in the service of the regime.

የአቡነ ጳውሎስ ሹመትና የቤተ ክህነቱ ባዲስ የሰው ኃይል መተካት

መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ በሆኑ በሶስት አመታቸው ‘’በህመም ምክንያት’’ በሚል ከስልጣን ወርደው አቡነ ጳውሎስ ስልጣኑን ተቆጣጠሩት። ከሳቸውም ስልጣን መያዝ ጋር ተያይዞ በርካታ አዳዲስ ‘’ካህናትና መነኮሳት’’ የቤተ ክህነቱ ሹመኞች ሆኑ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም ታይቶ በማይታወቅ መልኩም፤ አቡነ ጳውሎስ አዳዲስና ወጣት ጳጳሳትን መሾም ቀጠሉ። መረጃዎች እንደሚያሳዩት አቡነ ጳውሎስ በህይወታቸው እያሉ ከ40 በላይ ጳጳሳትን ሾመዋል። ይሄም በሁለት ሺህ አመት የቤተ ክርስቲያን ታሪኳ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ቁጥር ነበር። በመሰረቱ የጳጳሳት በብዛት መሾም በራሱ እንደ ችግር ላይቻል ይችላል። ነገር ግን ባቡነ ጳውሎስ የተሾሙት ጳጳሳት አብዛኞቹ ‘’የበረሃው ሲኖዶስ አባላትና የኅወሃት ስራ አስፈፃሚ’’ ሲሆኑ አላማቸውም ለመንፈሳዊው ጉዳይ ሳይሆን ፖለቲካ ዘመም ነበር።  ይህም በተለያዩ ግዜያት በተካሄዱ የሲኖዶስ ስብሰባዎች ታይቷል።
አሁንም እንደሚታየው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ተከፋፍሏል። ክፍፍሉም የሚታየው ነባሮቹ ጳጳሳትና አዲስ በተሾሙት ጳጳሳት መካከል ነው። ነባሮቹ ‘’ከፓትሪያርክ ምርጫ በፊት እርቁ ይቅደም’’  ሲሉ አዲሶቹ ‘’ባስቸኳይ ሌላ ፓትሪያርክ ይመረጥ’’የሚል የሃሳብ ጽንፍ ይዘው እየተሟገቱ ሰንብተዋል። በቁጥር አብላጫውን የያዙት አዲሶቹ ያባ ፓውሎስ ጳጳሳትና የበረሃው ሲኖዶ ምልምሎች ሲኖዶሱን እየተቆጣጠሩት ብቻ ሳይሆን በፍፁም ከቤተ ክርስቲያን ተሰምቶ የማያውቅ ድምፅ እያሰሙ ነው። በስብሰባው ላይ አንዱ የበረሃ ጳጳስ ያለ ሃፍረት እንዲህ ሲሉ ነበር የተናገሩት ‘’ፓትሪያርክ መርቆሪዎስ የሚመለሱ ከሆነ ትግራይ የራሷን ፓትሪያርክ ትሾማለች’’። እንግዲህ ጳጳሳት በመሆን በአቡነ ጳውሎስ ተሹመው ቤተ ሲኖዶሱን የተቀላቀሉት እንዲህ ዓይነት አባቶች ናቸው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ አይነት አደገኛ አጣብቂኝ  ውስጥ ገብታለች። የኅወሃት አምባሳደርና ካድሬዎች የነበሩ መነኮሳት ሲኖዶሱን እየተቆጣጠሩትና ሲኖዶሱንም የፖለቲከኞች ስራ ማስፈፀሚያ እያደረጉት ነው።

የማህበረ ቅዱሳን ፓትርያርክ

የሴራው መሀንዲሶች ይሄን እኩይ ስራቸውን ለመሸፈንና ራሳቸውን ከደሙ ንጹህ ለማስመሰል በርካታ ማጭበርብርያዎችን ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ከዚህም አንዱ ‘’ማህበረ ቅዱሳን የራሱን ፓትርያርክ ሊያስመርጥ እየተሯሯጠ’’ እንደሆነ ማስወራትና ሕዝቡን ለማደናገር መሞከር ነው። ይሄም አላማው ሁለት ነው። ባንድ በኩል ማሕበረ ቅዱሳንን በሕዝቡ ለማስጠላት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የፓትሪያርክ ሹመት ሹኩቻ ውስጥ መንግስት እጁ እንደሌለበትና መተራመሱ ያለው የተለያየ ዓላማ ባላቸው የቤተ ክርስቲያኗ አካል እንደሆነ ለማስመሰል ነው። ይሄንንም ከዳር ለማድረስ በተለይ ወያኔ በውጭው አለም ያሰማራቸው ሰላይና ቅጥረኛ ፀሐፊዎቹ ከፓትርያርክ ሽኩቻውና እርቀ ሰላሙ አለመሳካት ጀርባ ማሕበረ ቅዱሳን መኖሩንና ዓላማውም የራሱን ፓትርያርክ ማስመረጥ እንደሆነ ጆሮ አደንቁር የሆነ ጽሁፍ የወተቱ ጠቆረ፣ ማሩ መረረ ዘመቻውን አፋፍመውት ከርመዋል። የሚሰማቸውና የሚያምናቸው ባይኖርም።

ሌላ የጨለማና የውዝግብ ዘመን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን

የፖለቲካውን ጉዳይ ለማስፈፀም እንጂ ለቤተ ክርስቲያኗ እድገት ብዙም ደንታ ባልነበራቸው በአቡነ ጳውሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያኗ የተከታዮቿን ሰባት ፐርሰንት አጥታለች። በቀረውም መእመን ላይም ከባድ የሞራል፣ የስነ አእምሮና  ባባቶች ላይ ተስፋ ያማጣት ጉዳይ ተከስቷል።  ተጀምሮ የነበረው እርቀ ሰላምም መክሸፉ የብዙዎችን ልብ ሰብሯል። ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ግን አሁንም ቀጣይ የሚመረጡት ፓትርያርክ ጉዳይና ሁለቱም ሲኖዶሶች ውስጥ እየታየ ያለው ሃይማኖትን የመገዝገዝ አባዜ ነው። የውጭው ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያኗ የሀይማኖት ህጸጽ (ስህተትና ኑፋቄ)ተገኝቶባቸው ከቤተ ክርስቲያን ተለይተው የነበሩ መናፍቅ ሰባኪያንን በማወቅም ይሁን ጡንቻ ለማጠንከር እያስጠጋቸው ንው። አልፎ ተርፎም የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ እየታየ ነው። ከዚህም አልፎ የውጭው ሲኖዶስ በሚያስተዳድራቸው አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ‘’ዘመኑን ለመዋጀት’’ በሚል ሽፋን በቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና ላይ እንዳይውሉ የተደነገጉ እነ ኦርጋንና ፒያኖን የመሰሉ መሳርያዎች ገብተው የአምልኮውን መልክ እየቀየሩት ነው። የአዲስ አበባውም ሲኖዶስ የመንግስት undercover agents የሆኑ ጳጳሳት ተሰግስገውብውታል። እነዚህም ወገኖች አላማቸው የፖለቲካውን አጀንዳ ማስፈጸም እንጅ ሃይማኖትን ባለመሆኑ ለቤተ ክርስቲያኗም ሆነ ለመንጋው ደንታ የሌላቸው ጨካኞች ናቸው። ቤተ ክርስቲያኗ ከሁለት ወግን ተንጋላ እየታረደች ነው።
    
ለዚህ ሁሉ መሰረት የሆነውን ችግር ታላቁ ካናዳዊው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ቴዎዶር ቬስቴል ይህንን ጉዳይ እንዲህ ሲሉ ነበር ያስቀመጡት፤

This and other acts of violence in and around churches have alienated the patriarch from his spiritual flock and have contributed to the EPRDF goal of exploiting internal contradiction within the EOC leadership to weaken any opposition to the front.

ግን ወያኔ ለዘላለም ይኖር ይሆን? የቤተ ክርስቲያን አምላክ ሆይ ቤትን አጽዳ!

ማጣቀሻ መጽሐፍት

-   Berhe Aregawi, A Political History of the Tigray People’s Liberetion Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilization in Ethiopia

-   John Young, Peasant Revolution in Ethiopia: The Tigray People Liberation Front 1975-1991 Cambridge University Press 1977 pp 176

-   Lencho Leta, The Ethiopian State at the Crossroads, Red Sea Press


-   Theodore M. Vestal, Ethiopia: A Post-Cold War African State

No comments:

Post a Comment