Tuesday, February 19, 2013

የኢትዮጵያ ትምህርት ፖሊሲና ችግሮቹ


Author Baile Derseh
ባይሌ ደርሰህ ምህረቴ

ወያኔ በ21 ዓመት ቆይታው በትምህርት ፖሊሲው ላይ ይዞት የመጣው የኣንድ ቢሔር ብቻ የመጥቀም ኣላማውን ከግብ ለማድረስ በ1984ዓ ም ኣዲስ የትምህርት ፓሊሲ ቀርፆ 10ዓመት ባልሞላ ውስጥ ሶስት ጊዜ የመማሪያ መጽሐፍትን በመቀያየር ትምህርትን ከግዜ ወደ ግዜ ጥራቱ በማሽቆልቆል ዕነሆ ዛሬ ሞገደኛና በራሱ የማይተማመን ትውልድ ሊፈራ ችሏል። የወያኔን የትምህርት ፖሊሲ በተለያየ ጊዜ ያገባኛል የሚሉ መምህራን፤ተማሪዎችና ወላጆች የትምህርት ፖሊሲዎ ያለበትን ችግርና ያመጣዎን ኣሉታዎ ተግባር በተደገፈ መረጃ ቢያቀርቡም ወያኔ በማንኣለብኝነት ጥያቄዎን ለኣነሱ ሀገር ወዳድ ሙህራን ምላሹ ዕስራት፤ሞትና ስደት ገጥሟቸዋል።
ወያኔ ዕንደፈለገዎ በህዝብ ላይ ዕንዲፈነጭ ሲያደርጉት የነበሩ ምራባዊያን፤ኣሜሪካና ኣለም ባንክ ዛሬ ግን ችግሩ ኣፍጥጦ ወደ ራሳቸው ሲመጣ የችግሩን ኣሳሳቢነት በጥናትና ምርምር በተደገፈ ሰነድ በማስረዳትና ከሌሎች ኣገሮች ጋር በማወዳደር የኢትዮጰያ ትምህርት ፖሊሲ ከፍተኛ ችግር ያለበት መሆኑን በማጉላትና በዚሁ ከቀጠለ ሀገሪቱን ኣደጋ ላይ እንደሚጥላት እየገለጹ በኣስቸኳይ የሁሉም ክፍሎች የትምህርት ካሪኩለም መከለስና መለወጥ እንዳለበት ኣለም ባንክ ኣስጠነቀቀ።

ከዚህ በመቀጠል የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ፖሊሲ መለወጥን ኣስመልክቶ ኣለም ባንክ ያወጣውን ሪፖርት በማየትና የራሴን በስራ ዘመን በቆየሁባቸው ጊዜ የታዘብኋቸውን ኣንኳር ጉዳዮች ኣጭር ባጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ።

ኣለም ባንክ በዲሲ7፡2012 እ ኣ ሂልተን ሆቴል በሰጡት መግለጯ ኣንኴር ነገሮቸን ኣንስተዋል እነዚህ ኣንኳር ጉዳዮች መረጃን ድጋፍ ባደረገ በ221 ገጽና በ9 ምዕራፎች በተከፈለ የችግሩን ኣሳሳቢነት በማጉላት መንግስት በኣስቸኳይ ርዕምት እንዲወስድ ኣስጠንቅቋል። እኔም የችግሩ ኣካል የሆነዉን በመለየትና ዓለም ባንክ በጥናታቸዉ ያቀረቡትንና የራሴን ትዝብት በመጨመር ከዚህ በታች እንደሚከተለዉ ኣቀርባለሁ።

1. በክፍል ዉስጥ ያለዉን የተማሪ መጠን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዉስጥ ባንኩ በጥናቱ የኣገኘዉ በኣማካኝ 64 ተማረዎች ይበል እንጂ በኣንዳንድ ት/ቤቶች 100ና ከዚያ በላይ እንደሚገኙ የኣደባባይ ሚስጥር ነዉ።በኣንድ ወቅት ወደ ኣዋሳ ኣካባቢ ት/ቤቶችን ለመጐብኝት ዕድሉን ኣግኝቼ ነበርና የኣንድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎችን ቁጥር በክፍል ዉስጥ ምን ያህል እንደሆነ ርዕሰ መምህሩን ስጠይቀዉ ከ100 እሰከ 120ይደርሳሉ ኣለኝና ለመሆኑ ፈተና እንዴት ትሰጣላችሁ ብዩ ስጠይቀው ወረቀት እናባዛና ለእያንዳንዱ ተማሪ በመስጠት ዉጭ ሰርተው ይመጣሉ ሲለኝ እጅግ ተገርሜ ይህ ነው እንግዲህ ወያኔ ትምህርትን በጥሪትና በፍታዎነት እሰጣለሁ የተዛባ ሪፖሪት ለህዝብና ለኣለም ዓቀፍ ድርጅቶች ሲቦተልክ የቅየዉ፡ይህን የገዘፈ የተማሪ ቁጥር ዓለም ባንክ በጥናቱ ያረጋገጠና ችግሩም በኣስቸኳይ እርምት እንዲዎስድ ባንኩ ኣስጠንቅቋል።

2. የተማሪዎችን የዕድሜ መጠን ማነስ በተመለከተ፤

ወያኔ በራሱ ፍላጎት ተማሪዎችን፤መምህራንና የተማሪ ወላጆችን ሳያማክር እኔ ኣውቀዋለሁ በማላት ከ6፡2፡4 ወደ8፡2፡2 እና 3ዓመት ዪኒበርስቲ ቆይታ ግዜ በ1984ዓ ም የት/ ፖሊሲ ቀርፃል፤በዚህ የት/ፖሊሲ ምሁራን፤ ተማሪዎችና ወላጃች በተለያየ ጊዜ የፖሊሲዎን ችግር ሲያነሱ ቢቅይም ወያኔ የተለያየ ስም በመስጠት ለእስራትና ለስደት ዳርጔቸዋል።የመጀመሪያ/ ኣንኳር ችግር ብሎ ዓለም ባንክ በጥናቱ የዓረጋገጠዉ 10ኛ ክፍልን በ15ዓመት መጨረስና ወደ ቴክኒክ ሙያ ሲሄዱ የ1 ዓመት፤ የ2 ዓመትና የ3 ዓመት ስልጠና ወስደዉ ወደስራ ሲሰማሩ በዓለም ዓቀፍ ከተቀመጠዉ የእድሜ ክልል ማለትም ከ18 ዓመት በታች ስለሚሆኑ ይህ የት/ ፖሊሲ ችግር እንደለበት ዓለም ባንክ ያሰምርበታል።

3. በክፍል ውስጥ ያላቸው የተማሪዎች ተሳትፎ ኣናሳ መሆን፤

ከላይ ለምግለጽ እንደሞከርሁት ተማሪዎች ያልተቀበሉትና ያልተሳተፉበት የት/ ፖሊሲ በመሆኑ በክፍል ዉስጥ ያላቸዉ ተሳትፎ ኣሉታዎ መሆኑ በግልጽ ተማሪዎች በሚያመጧቸዉ ዉጤቶች መገንዘብ እንደሟቻል የ10ኛ ክፍል ፈተና ላይ 20% ብቻ ማለፋቸዉ በት/ ፓሊሲዎ ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩን ያመላክታል።

4. የመጽሐፍ ጥምርታን በተመለከተ፤
  • መጽሓፍት ወቅቱንና ግዚዎን ጠብቅ ኣለመስጠት በተማሪዎች ዉጤት የመጣዉ ኣሉታዊ ድርጊት ይገልጻል።
  • ጭራሽ መጽሓፍት ሳይታደሉ የት/ ዘመኑ መገባደዱና ማለቁ የተማሪዎችን ውጤት ማሽቅልቅል ምክንያት ሆኗል።
  • የመጽሓፍት ዕደላ በጋራ መሆን ተማሪዎች የቤት ስራቸዉን ሳይሰሩ በመምጣት በክፍል ውስጥ ትምህ ርቱ ለመከታተል ሲያዳግታቸዉ ይታያል።
5. ቤተሙከራ ኣለመኖሩ በተማሪዎች ዉጤት ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ኣምጥቷል፤
  • የቤተሙከሪዎ ህንጻው ሳይኖር ት/ቤት መክፈት
  • በቤተ ሙከራ ዉስጥ ምንም ኬሚካልና ኣፓራተስ ኣለመኖሩ
  • መምህራን በቤተሙከራ ያላቸው ብቃት ማነስ
  • የቤተ ሙከራ ክፍለ ጊዜ ኣለመኖር
  • ቤተ ሙከራ ክፍሎች ቢኖሩም ከተማሪዎች ቁጥር ጋር የተመጣጠነ አለመሆኑ
ከዚህ በላይ የተገለጹት ችግሮች በሳይንስ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽኖ አምጥቷል።

6. ቤተ መጽሃፈት አለመሟለት አንዱ የትምህርቱን ጥራት ውድቀት ነው
ይኽውም፤
  • ማጣቀሻ መጸሃፍት በግባቡ አለመገኘት
  • የቤተ መጸሃፍት ህንጻ ሳይኖር ት/ቤቶችን መክፈት
  • በሙያው የሰለጠነ ባለሙያ አለመኖር
7. የመማሪያ ክፍሎች ምቹ አለመሆን የትምህርቱን ውድቀት ሊያጎላው ችሏል
እነሱም፤
  • ት/ቤቶች ሲገነቡ የአካባቢውን የአየር ጸባይ ያገናዘበ ያለመሆን
  • የተማሪዎች መቀመጫ ያለመሟላት
  • በክፍል ውስጥ የተለያዩ ግብዓት ያለመሟላት
8. የትምህርት ማበልጸጊያ አለመኖር እና በሙያው ብቁ የሆነ መምህር አለመመደቡ የትምህርቱን ጥራት ሊያጎድለው ችሏል።

9. የካሪኩለሙ መክበድና ወደ ቀለም ትምህርት ማዘንበሉ ና የየክፍሉ ትምህርቶች ክህሎትን የሚያጎለብቱ አለመሆናቸው።

10. በየክፍሉ ባሉመጸሃፍትላይ ድግግሞሽ፤ ተከታታይነት የሌላቸው ይዘቶች መቀመጣቸው ና መጸሃፍት ሲዘጋጁ ሙያተኛን አለማሳተፍ

11. ደረጃዎን የጠበቀ ካሪኩለም ኣለመዘጋጀት በተማሪዎች፤በመምህራንና በወላጆች ላይ ኣሉታዎ ኣመላካከት ኣምጥቷል።ለምሳሌ ያህል የኣለም ባንክ በጥናቱ የጠቀሰዉ በእንግሊዝ ኣገር የሒሳብ ትምህርት ያለዉን ይዘት 3ኛ ክፍል ሲጀምሩት ኢትዮጵያ ይኽንኑ የትምህርት ይዘት 1ኛ ክፍል ይጀምራሉ ይላል ይህ ዓነቱ የትምህርት ፓሊሲ ደረጃዎን ያልጠበቀና የተማሪዎችን ኣቅም ያለገናዘበ በማለት ሲጠቅስ ወደፊትም መንግስት ሊያስብበት እንደሚገባ ያስጠነቅቃል።

12. የመምህራን የትምህርት ዝግጅት መብዛት መምህራን ትምህርቱን ከማንበብ ፈንታ ብዙን ግዜ የሚያሳልፍት የትምህርት ዝግጅት ሲያወጡ ነዉ።

13. ከኣቅም በላይ የመምህራን ክ/ግዜ መብዛት በተለይ በገጠር ኣካባቢ የሚያስተምሩ መምህራን በቀን ከ6እስከ 7 ፔሬድ በማስተማር የተጠመዱ መሆናቸው

14. የፆታ ክፍተት
  • ኣብዛኛውን85% የሆነው ህዝብ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እንደሟኖር ይታወቃል ከዚህ 85% ውስጥ ወደ ት/ቤት የሚመጡት ሴት እህቶቻችን ቁጥር ኣናሳ መሆን የፆታ ኢፍታውነቱን ኣጉልቶታል።
15. የመንግስትፓለቲካዊ ጫና በትምህርቱ ላይ የፈጠረው ኣሉታዊ
  • ት/ሚ የሰጠውን የትምህርት ጊዜ ሰለዳ በመንግስት ፖለቲከኛች በመዳጥ ለፖለቲካዊ ስብሰባ ቅድሚያ በመስጠት ት/ ቤቶችን በተለያየ ጊዚ ሲዘጉ ይታያሉ፡ ይህ ክፍተት መምህራን ትምህርቱን በወቅቱ እንዳይጨርሱ ስለሚያደርጋቸው በመማር ማስተማሩ ላይ ኣሉታዊ ውጤት ኣምጥቷል።
16. የመምህራን ጥቅማጥቅም ኣለመከበር በትምህርቱ ጥራት ላይ ውድቀት ኣስከትሏል
  • ትምህርት የኣንድ ሐገር የእደገት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑ እየታወቀ ወያኔ የራሱን ዕድሜ ማራዘሚያ የሆኑትን ሴክተሮች መርጦ ደሞዝ በመጨመር የትምህርቱን ዕድገት ቆልፎ ይዞታል።
  • ደሞዝ ከሌሎች ኣቻ የትምህርት ዝግጅት ጋር እኩል ኣለማግኝት
  • የትምህርት እድል ብሔርን ፤ ጐሳን ማእከል ማድረጉ
  • በገጠር ኣካባቢ ለሚገኙ መምህራን የመኖሪያ ቤት ባለመመቻቸቱ በተለይ ሴት መምህር እህቶቻችን በተለያየ ጊዜ ለወሲብ ጥቃት ሲጋለጡ ይታያሉ።
17. ተማሪዎችን ለፈተና ብቻ ማዘጋጀት /paper based test/ የትምህርት ፖሊሲው ተማሪዎች አካባቢያቸውን ወይም ሂወታቸውን ሊለውጥ በሚችል መልክ ባለመዘጋጀቱ ተማሪዎች ተስፋሲቆርጡና የትምህርት ጥቅም ጎልቶ አለመውጣቱ ይታያል። የአለም ባንክምየትምህርት ፖሊስዊ አካባቢያቸውን በሚያገናዝብ/ሂይዎታችውን/ ሊለውጥ በሚችልና ምርምር በሚያመጣ መንገድ እንዲዘስጋጅ አስጠንቅቌል።

18. መ ምህራን ለሙያቸው ተነሳሽነት አለማሳየት
  • መንግስት በሙያቸው ጣልቃ መግባት
  • መምህራን ለትምህርት ፖሊሲው እውቅና አለመስጠት
  • መንግስት የመምህራንን ሙያ ከሌሎች ሙያ አውርዶ ስላስቀመጠው
19. የህብረተሰብ ተሳትፎ አለመኖር
  • መንግስት ለራሱ የመረጠውን የትምህርት ፖሊሲ እደፋሽን በፈለገው ጊዜ በመቀያየር ና በመጫን የህብረተሰብ ተሳትፎ በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ገድቦታል።
20. የበጀት አመዳደብ ችግር
  • ፍትሃዊነት የጎደለው በጀት ማስቀመጥ
  • በጀት ሳይመድቡ ት/ቤቶችን መክፈት
  • በጀትን በተማሪ ቁጥር ሳይሆን በጎሳና በብሔር መመደብ
በነዚህና በሌሎችም ባልተጠቀሱ ምክናያቶች ኢትዮጲያ በአለምላይ ትምህርትን ጥቅም ላይ ያላዋለች አገር አድርጓታል። ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች መነሻ በማድረግ መወያሰድ ያለባችው እርምጃዏች ብሎ አለምባንክ ያስቀመጠውንና የራሴን አስተያየት እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ።
  • አዲስ የመጸሃፍት ዝግጅት በሁሉም የትምህርት ክፍሎች አካባቢያችውን በሚያገናዝብና ለሂይዎታችው ለውጥ በሚያመጣ መልኩ መዘጋጀት አለበት።
  • ካሪኩለሙ በኣዲስ መልክ መከለስን መስተካከል ካልተደረገ ከዝቅተኛ ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላት አገር በ2024/2025 መግባት እጅግ ያስቸግራታል/አለምባንክ/
  • የመምህራንን ሙያዊ ብቃት በተለያዪ ስልጠና ማጎልበት
  • የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን ምደባ በፖለቲካዊ መስፈርት ሳይሆን ሙያዊ ብቃትን ያማከለ መሆን አለበት
  • ቅድመ በጀትና እቅድ በአግባቡ ተዘጋጅቶ ት/ቤቶች መተዳደር አለባችው
  • ተማሪዎች አካባቢያቸውን ያገናዘበና የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያጎለብት የትምህርት ፖሊሲ መዘጋጀት አለበት /አለም ባንክ/
  • አላማ ያለው ካሪኩለም ማለትም ምን እሰራለሁ፤ ምን እሆናለሁ ብለው ተማሪዎች ራሳችውን የሚጠይቁበት ካሪኩለም መዘጋጀት አለበት/አለም ባንክ/
  • የት/ፖሊሲው ICT/information communication technology/ የሚያሳድግ መሆን አለበት/አለምባንክ/
  • የት/ፖሊሲው ፍትሃዊነትን መአከል ያደረገ መሆን አለበት
  • የመምህራን የስራክብር/professional recognition/ መስጠትና በሙያቸው ጣልቃ አለመግባት
  • የመምህራንን ጥቅማጥቅም ደሞዝ ደረጃ እድገት ህክምና ቤት ነጻ የትምህርትእድል በፍትሃዊነትመዳረስ አለበት
እነዚህንና ሌሎችንም ያልተጠቀሱትን ምክነያቶች በመመርመር ትምህርትን ከወደቀበት ማንሳት ካልተቻለ መንግስትበ2024/2025 ከዝቅተኛ ወደ መካከለኛ እገባለሁ ብሎ ያለመው ህልም ቅዠት ይሆናል።

የትምህርትን ጥራት እንጠብቅ!

No comments:

Post a Comment