Saturday, February 23, 2013

ESAT Kignit (ቅኝት) OSLO/Norway - Artist Tamagn Beyene Part II 22 February 2013 Ethiopia

 

በታዋቂውና ተወዳጁ አርቲስትና አክትቪስት ታማኝ በየነ መሪነት በኖርዌይ በተዘጋጀው የኢሣት ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኝና በኖርዌይ (ኦስሎ) ነዋሪ የሆኑት አቶ የሱፍ ያሲን ነፃ ሜዲያ ለዴሞክራሲ ግንባታ ስለሚጫወተው ሚና አልጃዜራ የዓረብ ቴሌቪዥንን እና ነፃና የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ አንዲሁም ልሣን የሆነውን የኢትዮጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ስርጭትን (ኢሣት) በማነፃፀር የሰጡት ሰፋ ያለና ጥልቅ ማብራሪያ ላይ እንዳለ የተወሰደ መነበብ ያለበት፦
‘’ኢሳት ይህንን የምንላቸውን ተልዕኮዎች እየፈፀመ፤ አሁን የምንላቸውን ተልዕኮዎች ማለት ሚዛናዊ የሆነ መረጃ ማቅረብ፤ በዛ ሚዛናዊ የሆነ መረጃ ላይ ተመስርቶ ትክክለኛ የሆነ ነፃ እድምተኛ ኖሮት፤ ትክክለኛ የሆነ አደረጃጀት ኖሮት፤  ትክክለኛ የሆነውን ደግሞ መግባባት የሚፈጠርበት ሁኔታ መፍጠር ነው።
ከሁሉም በላይ ግን፣ ከሁሉም በላይ ግን አልጃዚራ ለዓረቡ ዓለም ያስተማረው አንድ ነገር ቢኖር ምንድ ነው፤ በቦክስም፣ በዱላም፣ በሽጉጥም፣ በሌላም፣ በሌላም እየተፋለሙ አንድ ነገር ተምረዋል። ያም ምን ማለት ነው፤ አንድ ሃሣብ የማንሸራሸርና የመግባባት ባህል፣ ውይይት ካልቸር መፍጠር ነው። እኛ ይህን የግድ መፍጠር አለብን። ይህንን መፍጠር ካልቻልን፤ ይህንን ሃሣብ የማንሸራሸር፤  እየተቧቀስንም፤ እየተጣላንም ይህንን መፍጠር እስካልቻልን ድረስ ነገ ተነገወዲያ ይኼ መንግስት በሚወገድበት ግዜም ጭምር መግባባት ላይ ካልደረስን፤ ዛሬ በዓረቡ ዓለም የተደረገው መነሣሣትና መንግስታት ከተወገዱ በኋላ ያለውን የሽግግር አሽቸጋሪነት፣ የሽግግር ውስብስብነት፣ የሽግግሩን አንዳንድ ቦታ እስከነ ጭራሹ ወደ እርስ በርስ ጦርነት የሚያመራበት ሁኔታ ስለምንመለከት፤ ይህንን የሃሳብ የማንሸራሸሩ ሂደት የግድ መሆን ያለበት ወሳኝ ጉዳይ ነው።
ለዚህም ነው ዛሬ እዚህ ያሉትንና በተለይ በመካከላችን የተገኘውን ታማኝ በየነን ይህንን ለነገ የማይባልና አገራችን በምንገባበት ግዜ የምንማማረው ሳይሆን፤ እዚህ ሆነን፣ ውጪ ሆነን መማማር ያለብንን ጉዳይ አደራ እናሸክመዋለን ማለት ነው።
እንዳልኩት እነ ታማኝ እንግዲህ ጆርናሊስት ሳይሆኑ አክትቪስት ብለው መንግስት ጋር ጆርናሊዝምና ነፃ ሃሣብ የሚያራምዱ ኃይሎች የገቡት ግብግብ ምክንያት ነው አንግዲህ በጠላትነት የተፈረጁት።’’
 
 
ESAT Kignit (ቅኝት) OSLO/Norway - Artist Tamagn Beyene Part II 22 February 2013 Ethiopia 
 
 

No comments:

Post a Comment