February 4, 2013
“የኢህአዴግ
ስርአት መወገድ አለበት፤ ሙሉ ጊዜዬን ለፖለቲካ ስራ በማዋል ስርአቱን ለመታገል ተዘጋጅቻለሁ” ሀብታሙ አያሌው
ላለፈው አንድ አመት የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ሀብታሙ አያሌው ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው በማስመሰል በኢሜልና በስልክ የማያውቃቸው መልዕክቶች እየደረሱት እንደሆነ ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡
በፈጠራ መረጃዎች ብዙዎች እንደታሰሩ
ያስታወሰው ሀብታሙ ከዚህ መልዕክት ጀርባ በስውር የሚንቀሳቀሱ የመንግስት የደህንነት ሀይሎች እጅ እንዳለበት እንደሚያምን
አስረድቷል፡፡ አያይዞም ያለው ስብዕናና ሀይማኖታዊ አስተዳደግ ከሽብርና ጥፋት ሊያቀራርበው እንደማይችል ተናግሯል፡፡
የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አባላትን
“እንዴት ከሀብታሙ ጋር ትሆናላችሁ እሱ ከ ግንቦት ሰባት ጋር ግነኙነት አለው” በማለት በመንግስት ደህንነት ሀይሎች ሀሰተኛ
ውንጀላ እየቀረበብኝ ነው በማለት አስረድቷል፡፡ ጨምሮም የማህበሩ አባላት የመንግስት ካድሬዎችና ደህንነቶችን ሴራ ለማጋነጥ እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጧል፡፡
አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በሲቪክ
ተቋማት ተደራጅቶ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎ እንደማያምን የገለፀው ሀብታሙ አያሌው “የኢህአዴግ ስርአት መወገድ አለበት፤ ሙሉ
ጊዜዬን ለፖለቲካ ስራ በማዋል ስርአቱን ለመታገል ተዘጋጅቻለሁ” ብሏል፡፡
No comments:
Post a Comment